አንቀጽ 1 Article I
የዋስትና ዕድር ምስረታ
The establishing of Wastena (WMSA)
1.1 የዕድሩ አላማና የተመሰረተበት ምክንያት
1.1 Objective and reasons for establishing WMSA
በካናዳ ኦንታሪዮ ክፍለሀገር በቶሮንቶ ከተማና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች ተቀራራቢ ባህል ያላቸው አንድ የህብረተሰብ አባል ከዚህ አለም በሞት ሲለያቸው ለቀብሩ ማስፈጸሚያ የሚወጣው የገንዘብ መጠን ለአንድ ሰው ወይንም ለቤተሰቡ ከአቅም በላይ እየሆነ መጥቶአል፡፡ ፎቶ ግራፍ በሳጥን ላይ ለጥፎ በየንግድ ቤቱ፣ በየሃይማኖት ተቋሞችና በመሳሰሉት ድርጅት ውስጥ ለቀብር የሚሆን አስፈላጊው የገንዘብ መጠን እስኪሰበሰብ ድረስ የሟች አስከሬንን ሳይቀበር ለረጅም ቀናት በማቆየት ከዚያም አልፎ ተርፎ ወደ ተለያዩ ተቋሞችና ድርጅቶች እንዲሁም ወደ ግለሰቦች ቤት በማምራት ከባህላችን ውጭ በሆነ ተግባር ላይ ከተሰማራን ውለን ከርመናል፡፡ ይህንን ከፍተኛ ችግር ለማቃለል ይቻል ዘንድ የዋስትና ዕድር ቀለል ባለና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ባሳተፈ መልኩ በዚህ ደንብ ውስጥ የተገለጸውን የገንዘብ መጠን በማዋጣት የሟቹን የቀብር ስነ ስርዓት በክብር ለማስፈጸም ይረዳ ዘንድ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መሠረተ ሃሳቦች ላይ በመመርኮዝ በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት እድሩ ሊቋቋም ችሏል።
Ethiopians and others with similar cultures who are residing in Toronto and the surrounding regions in Ontario, Canada have been observed struggling to afford funeral expense on the death of a member in the community. Funeral expenses have been beyond the ability of individuals and families. There has been posting of the photographs of the deceased individual in a box and soliciting money from the community by displaying the boxes in various business/stores, religious institutions etc. since the funeral expenses are very high that one family could not afford. Furthermore, due to the financial hurdles, people were also forced to keep the bodies of the deceased individual for a longer time. Thus, to provide the community with a solution to address such kind of hardships, WMSA is established by the participation of community members who are willing to pay contributions as stated in this by-law, which is drafted based on basic rules and regulations.
ይህ ዕድር ከዚህ አለም በሞት ከሚለዩ አባላት መዋጮ በስተቀር ሌሎች ለተለያዩ ምክንያቶች ወይንም ችግሮች የዕድሩን ዓባላትን ገንዘብ እንዲያሰባስቡ አያደርግም
WMSA is not asking members to contribute money for any other reasons or problems except for the death of a member.
ይህ ዕድር ከሃይማኖት ፣ ከፖለቲካ፣ ወዘተ ነጻ ሲሆን ከዕድሩ አላማ ውጭ የሆኑ ማናቸውንም ነገሮች አያስተናግድም፡፡
WMSA does not accommodate religious, political and other matters that are beyond its objectives.
1.2 የዋስትና ዕድር የተቋቋመበት ቀን
1.2 Date of Establishment of WMSA
ይህ ዕድር ከዛሬ Dec 3/2017 ጀምሮ በቶሮንቶ ካናዳ፣ በካናዳ ህግ መሰረት ከትርፍ ነጻ በሆነ ድርጅት ስም ተመዝግቦ ተቋቁሟል፡፡
WMSA is established as of today Dec 3/2017 in Toronto, Canada as a nonprofit organization according to Canadian Law.
አንቀጽ 2 Article II
የዋስትና ዕድር መመዝገቢያ፣ መዋጮ፣ ክፍያ፣ የስራ ማስኬጃና የአባላት ቁጥር (ብዛት)
Registration fee, contribution, payout, expenses and membership size
2.1 የዋስትና ዕድር መመዝገቢያ፣
2.1 Registration fee
የዋስትና ዕድር አባል ለመሆን በዕድሩ መተዳደሪያ መሰረት መመዝገቢያ $125 የካናዳ ብር ነው፡፡
The registration fee for Wastena membership is $125 Canadian dollars per the by-law
2.2 መዋጮ
2.2 Member’s contribution
የዕድሩ አባል በሞት ሲለይ በተደነገገው ደንብ መሰረት እያንዳንዱ አባል $25 የካናዳ ብር በዋስትና ዕድር የሂሳብ ቁጥር ውስጥ ገቢ በማድረግ ይከፍላል፡፡
When a member of Wastena passes away, each member shall pay $25 (Canadian dollars) by depositing the amount in Wastenas bank account.
2.3 ክፍያ
2.3 Payout
አንድ የዕድር አባል በሞት ሲለይ ወራሾች እንደቅደም ተከተላቸው የአባሉን የሞት ማስረጃ፣ የሟቹን የአባልነት መታወቂያ እንዲሁም የሟቹ ወራሽ ማንነቱን የሚገልጽ ፎቶግራፍ ያለበት መታወቂያ ፎቶ ኮፒና ዋናውን ይዞ በመቅረብ አስፈላጊውን ፎርም ሞልቶ በወቅቱ በለው የአባላት ቁጥር ልክ የሚሰበሰበውን በቼክ ይከፈለዋል፡፡ የወራሹ የመታወቂያ ኮፒ በዕድሩ መዝገብ ላይ ይቀመጣል፡፡ወራሽ (ወራሾች) በአካል ቀርበው ገንዘቡን መውሰድ ባይችሉ ህጋዊ ውክልና ለሰጡት ሰው ወይም ተቌም ይሰጣል። (የሚሰበሰበው $25 በሰው ሲሆን $5 ብር ለስራ ማስኬጃ ይቀመጣል።
When a member of Wastena passes away, the beneficiary shall present the death document, members ID and beneficiary’s photo identification (original and a copy). Upon filing the required forms the collected Canadian dollar will be paid by cheque to the beneficiary. Copy of beneficiary’s identification will be kept in Wastena’s archive. If the beneficiary is not present the WASTENA mutual support association will pay according to the order of the second beneficiary or their representative.
2.4 ስራ ማስኬጃ
2.4 Expenses
የዕድር አባል በሞት ስለይ እያንዳንዱ አባል ከሚያዋጣው $25 (ሃያ አምስት ዶላር) ላይ $ 5.00 ( አስምት ዶላር) ተቀንሶ ለሥራ ማስኬጃ ይቀመጣል። ማንኛውም የዋስትና ወጪ በሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላት ተወስኖ በዕድሩ ፕሬዝዳንት በተፈረመ ደብዳቤ ትዕዛዝ ገንዘቡ በቼክ ብቻ ይከፈላል።
When a member of Wastena passes away, each members will contribute $25 dollar each and the $5 dollar will be dedacted to cover operationl expenses. If any expense occurs, the executieve commmitte has to authorize the payment followed by written order signed by WASTENA committee president and the payment will be by cheque only.
2.5 የአባላት ቁጥር (ብዛት)
2.5 Membership size
የአባላት ቁጥር ለጊዜው 1000 ተብሎ ይገመታል:: እድሩ ግን ሥራውን March 31, 2020, ባለው የአባላት ቁጥር ይጀምራል አባል ሲሞት የሚዋጣው በሕጉ የተደነገገው $25 እንደተጠበቀ ሆኖ ለሟች ቤተሰብ የሚከፈለው በወቅቱ ካለው አባል የሚሰበው ይሆናል::
Membership is expected to be 1,000. WASTENA will start paying out starting March 31, 2020, for the beneficiaries only from the collection of existing members.
አንቀጽ 3 Article III
የዋስትና ዕድር አባል፣ የዋስትና ዕድር አባል ወራሽ፣ የዋስትና አባል ተወካይ፣ የዋስትና ቡድን፣ የዋስትና የቡድን ሃላፊ
WMSA member, Beneficiary, WMSA member’s representative, Wastena (WMSA) team, WMSA team leader
3.1 የዋስትና ዕድር አባል
3.1 WMSA member
የዕድሩን አላማ የተቀበለ፣ ቃል ኪዳን የፈጸመ፣ በመተዳደሪያ ደንቡ ወስጥ የተጠቀሱትን ህጎች የሚያከብር፣ በአባልነት በዕድሩ መዝገብ ላይ ሙሉ ስምና አድራሻው የተመዘገበና በዕድሩ ሥራ አስኪያጅ አባላት ፊርማ የጸደቀ ነው።
An individual who swears under oath and recognizes the objective of the WMSA and agrees to the terms stated in the bylaw and has been registered as a member and has been confirmed/approved by the executive committee of the WMSA.
3.2 ወራሽ
3.2 Beneficiary
የዋስትና አባል በዕድሩ ድንብ መሰረት የአባልነቱን ቅጽ ሲሞላ ሞት ቢያጋጥመው የቀብሩን ሥነ ሥርዓት የሚፈጽምለት ብሎም ከዕድሩ የሚከፈለውን ጠቅላላ ክፍያ እንዲረከብ ውክልና የተሰጠው ግለሰብ ማለት ነው፡፡
Beneficiary and emergency contact: Members assigned as a beneficiary/emergency contact person is one that has been assigned as a beneficiary to take care of the deceased member’s funeral service and to receive payments from the WMSA.
3.3 የዋስትና አባል ተወካይ
3.3 WMSA member’s representative
የዕድሩ አባል በተለየ አጋጣሚ በአካል ከአካባቢው ቢርቅና ክፍያን ለመፈጸም ባይችል እንደራሱ ሆኖ ክፍያውንም ሆነ ሌሎች ጉዳዮችን እንዲያስፈጽምለት የወከለው ግለሰብ የአባል ወኪል (ተወካይ) በመባል ይታወቃል።
When a member of Wastena (WMSA) is not available to make payments due to various reasons/incidents such as moving etc. the person assigned by the member to make payments and perform other related tasks on behalf of him/her will be called member’s representative.
3.4 የዋስትና ዕድር ቡድን
3.4 Wastena (WMSA) team
የዋስትና ዕድር የግንኙነት መስመር ይቀላጠፍ ዘንድ ለእያንዳንዱ አባል በሃያ (20) የአባላት ቁጥር የተደራጀበት ምድብ የዋስትና ቡድን ተብሎ ይታወቃል።
To provide Wastena with a fast and reliable means of communication, a group consisting of 20 members has been formed. This group consisting of 20 individual members is called a team.
3.5 የዋስትና የቡድን ሃላፊ
3.5 Wastena (WMSA) team leader
በዋስትና መረዳጃ ዕድር ውስት በሃያ (20) አባላት ብዛት የተመደበውን ቡድን በሃላፊነት የሚሰራው አባል የቡድን ሃላፊ በመባል ይታወቃል
The individual/officer who is in charge of a team that’s composed of 20 members is called team leader.
አንቀጽ 4 Article IV
ስምና አርማን ስለመጠበቅ
Ownership of name and logo
የዕድሩ ስምና አርማ በእያንዳንዱ አባላት መታወቂያ ደብተር፣ የዕድሩ ደረሰኞችና በመሳሰሉት ሰነዶች ሁሉ ላይ ይቀመጣል፡፡ ይህ የመረዳጃ ዕድር የስምና የዓርማው ብቸኛ ተጠቃሚ ባለቤት ሲሆን ማንኛውም ሰው ወይንም ድርጅት ይህንን ስምና አርማ በማስመሰል፣ በመለወጥ፣ ቃላት በመቀነስም ሆነ በመጨመር ለግል ጥቅማቸው ወይንም ለማንኛውም ድርጅት ስራ ማራመጃነት መጠቀም በህግ ተከለከለ ነው::
The Name and logo of WMSA will be placed on each member’s identification card, receipts, as well as on other WMSA documents. WMSA is a sole proprietor of the name and logo. Any individual or organization cannot use the name and the logo by copying, amending and altering in any manner to benefit their interest as it is prohibited by law.
አንቀጽ 5 Article V
የአስተዳደር ኮሚቴ
Administrative committee
የዋስትና ዕድር የአስተዳደር ኮሚቴ አንድ ሰብሳቢ፣ አንድ ምክትል ሰብሳቢ፣ አንድ ጸሃፊ፣ አንድ ገንዝብ ያዥ፣ አንድ ኦዲተር፣ ኣንድ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊና አንድ አስተባባሪ ባጠቃላይ 7 የኮሚቴ አባላትን በመያዝ የዕድሩን የስራ እንቅስቃሴ በመከፋፈልና በመረዳዳት እንደ አንድ አካል በጋራ እየተንቀሳቀሱ የዕድሩን ሥራ በበላይነት የሚመሩ ሲሆን ቁጥራቸው እንደአስፈላጊነቱ ሊጨምር ወይንም ሊቀንስ ይችላል።
WMSA’s administrative committee is composed of a chairperson, a deputy chairperson, a secretary, a treasurer, an auditor, a public relations officer and a coordinator which is a total of seven committee members. These committee members will cooperate and run the WMSA. The number of committee members may increase or decrease as needed.
አንቀጽ 6 Article VI
የዋስትና ዕድር አባል ለመሆን የሚያስፈልጉት መስፈርቶች
Membership requirements of WMSA
6.1 ማንኛውም ግለሰብ ዕድሜው ከአስራ ስምንት (18) ዓመት በላይ የሆነና ነዋሪነቱ በኦንታሪዬና አካባቢው የሆነ የዕድሩን ዓላማ በመረዳት ወዶ በፈቃዱ የተቀበለ ዕድሩ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት ፍቃደኛ የሆነና እራሱን ለዕድሩ ህግ ለማስገዛት የወሰነ ማንኛውም ሰው ሁሉ ዕድሩ የተቋቋመበትን መርሆዎች፤ ለወገኔ እደርሳለሁ፣እራሴን አዛለሁ፣ ሞትን አስባለሁ፣ ቃሌን አከብራለሁ በማለት እራሱን ለገባበት ቃል ኪዳን ለማስገዛት የወሰነ ሁሉ የዋስትና መረዳጃ ዕድር አባል መሆን ይችላል።
6.1. Any individual who is over the age of 18 and who is residing in Ontario and the vicinity can be a member upon the recognition of the objectives and the requirements of membership in WMSA and agreeing to abide by the by-law and the terms and conditions stated in it. The individual should also be willing to fulfill pledges and promises that are given to WMSA.
6.2 ማንኛውም ሰው በዘሩ፣ በጾታው፣ በሃይማኖቱ፣ በሥራውና፣ በፖለቲካ አመለካከቱና ምክንያት የዕድር አባል ከመሆን አይከለከልም።
6.2. No individual will be denied membership based on race, gender, religion, occupation and political view.
6.3 ማንኛውም አባል በቶሮንቶና አካባቢው መታወቂው ላይ ባለው ስምና መረጃ መሰረት በግንባር ቀርቦ የአባልነቱን ቅጽ መሙላት አለበት::
6.3. Any interested individual should appear in person with his identification card and fill out the membership registration form.
6.4 ማንኛውም ሰው የዕድሩ አባል መሆኑ የሚያረጋግጠው የዕድሩን የአባልነት ፎርሙን ሲሞላ፣ የመመዝገቢያ ክፍያውን አጠናቆ ሲከፍልና የአባልነት መታወቂያ በአካል ቀርቦ ሲወስድ ብቻ ነው።
6.4. The membership of any individual is confirmed upon filling up membership forms, paying the registration fee and obtaining membership identification cards in person.
6.4.1. አዲስአባል የ90 ቀን የቆይታ ጊዜውን ሲጨርስ ማለትም ከ91ኛው ቀን ጀምሮ በሞት ቢለይ ቤተሰቡ በዕድሩ ደንብ መሰረት ክፍያ ይሰጠዋል፡፡ 90 ቀን ከመሙላቱ በፊት ሌላ አባል ቢሞት ቢለይ $25 ( ሃያ አምስት የካናዳ ዶላር) የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
6.4.1. There is a 90 days waiting period for a new member, and the benefit starts on the 91st date. If another member dies before the waiting period is over, the member has to pay the $25 (twenty-five Canadian dollars).
አንቀጽ 7 Article VII
የአባልን ሞት ለዕድሩ ጽህፈት ቤት ስለማሳወቅ
Reporting the death of a member to the WMSA office
7.1 አንድ የዋስትና ዕድር አባል ከቅርብም ሆነ ከሩቅ ከዚህ አለም በሞት ሲለይ ሟቹ የዋስትና ዕድር አባል መሆኑንን ማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ማንኛውም የዕድሩ አባል የራሱን ስምና የአባልነቱን ቁጥር በመግለጽ ለዕድሩ ጽህፈት ቤት ማሳወቅ ይኖርበታል። አንድ የዋስትና አባል ሲሞት ይህንኑ ሁኔታ ከዕድሩ ውጭ የሆነ ሰው ሲያሳውቅ የሟቹን ስምና የመታወቂያ ቁጥሩን ለዕድሩ ጽህፈት ቤት መግለጽ ይኖርበታል። ነገር ግን የአባሉ ወራሽ የሆነው ግለሰብ በአካል በመቅረብ ዕድርተኛው መሞቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በመያዝ አስፈላጊውን ቅጽ መሙላት አለበት።
7.1. When a member of WMSA dies, any other member who could confirm that the deceased is a member of the WMSA can report the incident to the WMSA office by stating his/her name and membership number. If other individuals who are not members of the WMSA report death of a member to the office, the individuals should notify the office the name and id number of the deceased member. The beneficiary of the deceased should submit the death certificate evidence from funeral home to receive the benefits.
7.2 አባሉ የሞተው በቶሮንቶና አካባቢው ከሆነ እጅግ ቢዘገይ በአስራአምስት (15) ቀን ውስጥ የሞት ማስረጃ ለጽ/ቤቱ መቅረብ አለበት።
7.2. If the member dies in the Toronto and the vicinity, the death should be reported and the death certificate should be submitted to the WMSA office within a maximum of 15 days.
7.3 አባሉ የሞተው ከካናዳ ውጭ በሰሜን አሜሪካ ከሆነ በሃያ (20) ቀን ውስጥ የሞት ማስረጃ ለዕድሩ ጽህፈት ቤት መቅረብ የኖርበታል፡፡
7.3. If the individual dies outside Canada but in North America, then the death should be reported the death certificate should be submitted to the WMSA office within 20 days.
7.4 አባሉ የሞተው ከሰሜን አሜሪካ ውጭ ከሆነ ተወካዩ ወይም ወራሹ ወዲያውኑ ማሳወቅና በ30 ቀናት ውስጥ የሞቱ ሪፖርትና ማስረጃ ለዕድሩ ጽህፈት ቤት መቅረብ ይኖርበታል።
7.4. If the member dies outside of North America, the death should be reported immediately and the death certificate should be submitted to the office in 30 days.
አንቀጽ 8 Article VIII
የአባልን ሞት ለጠቅላላ አባላት ስለማሳወቅ
Announcing the death of a member to all members
8.1 የዋስትና ዕድር ጽህፈት ቤት የአንድ አባልን ሞት እንደሰማ ስለ ሪፖርቱ እውነተኛነት ማረጋገጥና ሁኔታውን በአስቸኳይ ለስራ አስኪያጅ ኮሚቴ መሪዎች በማሳወቅ አባላቶች በግዜው ግዴታቸውን እንዲወጡ ያደርጋል።
8.1 WMSA office will immediately verify the accuracy of a death report and then will notify the Executive Committee of the reported death so that members can pay their due in a timely manner.
8.2. በተጨማሪም የሟች ተጠሪ (ወራሽ) ፎቶግራፍ እንዳይወጣ እስካላስታወቁ ድረስ የዕድሩ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም የሟችን ማንነት የሚገልጽ ፎቶ ግራፍን ጠቅላላው አባል እንዲያውቁ ያደርጋል ።
8.2. In addition, unless the beneficiary notify not to post the photo the WMSA office will submit a picture of the deceased member to the Executive Committee using various mass media.
አንቀጽ 9 Article IX
የመመዝገቢያ ጣቢያዎች
Registration locations
ወደ ፊት ለጠቅላላ አባላቱ አመቺነትና እንደ ንግድ ባለቤቶች ፍቃደኝነት የመመዝገቢያ ጣቢያዎች በዝርዝር ይነገራሉ።
In the future Registration, locations will be disclosed to all members. The locations will be determined according to convenience to members and willingness of the business owners.
አንቀጽ 10 Article X
የአባላት የክፍያ ጊዜ ገደብ
Member’s payment due date
10.1 አንድ አባል ከዚህ ዓለም በሞት በሚለይበት ጊዜ ዜናው ለዕድርተኞች በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አስራ አምስት (15) ቀን ድረስ ዕድርተኞች በዋስትና የባንክ ሂሳብ ውስጥ በማስገባት መክፈል አለባቸው፡፡
10.1 When a member dies, the death will be announced using various mass media and members should make their payment within the grace period of 15 days in Wastena’s bank account.
አንቀጽ 11 Article XI
ከዕድሩ አባልነት መሰናበት
Termination of membership
ማንኛውም አባል ክፍያውን በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ የማጠናቀቅ ግዴታ አለበት፡፡ ነገር ግን ክፍያውን በ 15 ቀን ውስጥ ካላጠናቀቀ ከዕድሩ በፍቃዱ ተሰናብቷል ተብሎ ይወሰዳል፡፡
Any member of the WMSA has a duty to make the payment/contribution within 15 days. Failure to do so will be considered as a self-termination by the member.
አንቀጽ 12 Article XII
ውክልና መስጠት
Granting power of attorney
ማንኛውም አባል በቅርብ እያለም ሆነ ርቆ ሲሄድ የሚፈልገውን ሰው እንደራሱ አድርጎ ሊወክል ይችላል ሆኖም ተወካይ ባልፈጸመው ግዴታ አባሉ ከመጠየቅ አይድንም፡፡
Any member has the right to delegate a proxy that will act on his/her behalf; however, the member will be responsible for any failure committed by his/her proxy.
አንቀጽ 13 Article XIII
ከአባልነት ለመታገድ ያሚያስችሉ ሁኔታዎች
Conditions of membership termination
አንድ የዕድሩ አባል በዚህ ደንብ ውስጥ ያሉትን ግዴታዎች ባለመፈጸም ወይንም የዕድሩን ህልውና የሚያናጋ፣ የሚያፈርስና ብሎም የሚጎዳ፣ አባላትን የሚከፋፍልና የሚበትን ድርጊትን ሲፈጽም ከተገኘ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ጥሪ አድርጎለት እንዲመከር ይደረጋል። ነገር ግን ይህንን ሁሉ ህግ ጥሶ ከተገኘ ከዕድሩ በደብዳቤ ይሰናበታል፡፡ ከመሰናበቱም በፊት በነበሩት ማንኛውም ጉዳዮች ዕድሩን መጠየቅ አይችልም። ገንዘብም አይመለስለትም፡፡
If any member fails to fulfill his obligations as stated in the bylaw or if any member is found to be working against the interest of the WMSA, such as activities that jeopardise the existence of the association, then the member will be reprimanded by the executive committee. If the member continues to break the rules, he/she will be terminated and will not be able to claim anything from the WMSA.
አንቀጽ 14 Article XIV
በራስ ፍቃድ ከዕድሩ መሰናበት
Voluntary termination of membership
ማንኛውም አባል በማንኛውም ጊዜና ሰዓት አባልነቱን ማቋረጥ ይችላል ነገር ግን የዕድሩን መታወቂያ መመለስ ይኖርበታል፡፡ ስለመሰናበቱም በጽሁፍ ለእድሩ ጽህፈት ቤት ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
Any member of WMSA can discontinue membership any time, but he/she has to return their identification card. He/she also has to notify the WMSA in writing.
አንቀጽ 15 Article XV
በዕድሩ ላይ ተደራራቢና (ተከታታይ) ሞት በደረሰ ጊዜ
When repetitive death occurs to members of the WMSA
በሁኔታዎች አጋጣሚ ከሁለት አባላት በላይ በተመሳሳይ ቀን ወይንም በአንድ ሳምንት ውስጥ የሞት አደጋ ቢያጋጥም በዚህ ህግ ደንብ ውስጥ ያለው የክፍያ መጠን እንደተጠበቀ ሆኖ ለወራሽ ይከፈላል፡፡ ነገር ግን በአንድ ጊዜ መዋጮውን ለመክፈል አቅሙ ላልፈቀደለት አባል ስራ አስኪያጅ ኮሚቴው የአከፋፈሉን ቀናት ሊያራዝምለት ይችላል፡፡
In a situation where two or more members die on the same day or within one week, payments will be made exactly as indicated in the bylaw. If a member cannot afford to pay the contribution at the given time, the executive committee will make an exception to extend the time limit.
አንቀጽ 16 Article XVI
የዕድሩ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ
WMSA’s receipts
የእድሩ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ የዋስትና ዕድር ዓርማን የያዘ ይሆናል።
Wastena’s receipts will bear the logo of WMSA.
አንቀጽ 17 Article XVII
የዕድሩ አባላትን ጠቅላላ ቁጥር ለአባላት ማሳወቅ
Notification of total membership
የዋስትና ዕድር የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ በየጊዜው የዕድሩ አባላትን ጠቅላላ ቁጥር ለአባላት ያሳውቃል። The WMSA executive committee will provide the number of WMSA members to the general membership.
አንቀጽ 18 Article XVIII
ቤተሰብ የሌለው የዕድሩ አባል በሞት በሚለይበት ጊዜ
The death of a member who does not have family
18.1 አንድ የዋስትና ዕድር አባል የቅርብ ቤተሰብ ሳይኖረው በሞት በተለየ ጊዜ የእድሩ ጽህፈት ቤት የአስተዳደር ኮሚቴው አባላት በአስቸኳይ እንደ ሟች ቤተሰብ ሆነው የሚያገለግሉ ኮሚቴዎችን ያዋቅራሉ።
18.1 When a member of the WMSA who does not have immediate family dies, then the WMSA office will immediately assign a committee that will work on behalf of the deceased family.
18.2 የተዋቀረው ኮሚቴ አቅሙ በፈቀደው መሠረት በዋስትና ዕድር ኮሚቴ አመራር ስርጭት በሃሳብም በጉልበትም በመርዳት ቀብሩን ያስፈጽማል።ሥራ አስኪያጅ ኮሚቴውም አፈጻጸሙን ለአባላት ያውቃል።
18.2 The assigned committee will receive directions from WMSA committee perform the funeral process and WMSA committee will report to members.
አንቀጽ 19 Article XIX
የዕድሩ ጠቅላላ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባንና የድምጽ አሰጣጥን ሥርዓት
Annual General Meeting and voting
19.1 የዋስትና ዕድር ጠቅላላ ጉባዔ በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ይሆናል። በሚገኘው አባል አስፈላጊው ውይይት ውሳኔ ይደረጋል።
19.1 The general meeting of WMSA will be once a year. The present members and the committee discuss and decide if any decision is needed.
19.2 የጠቅላላ ጉባኤውን ውሳኔ የሚሹና ጊዜ የማይሰጡ አንገብጋቢ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ለሥራ አስኪያጅ ኮሚቴው ይቀርባል
19.2 When important issues that require decisions by the general meeting arise it will be sent directly to the executive committee.
19.3 ከግማሽ በላይ የሚሆኑ አባላት ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ ሊጠይቁ ይችላሉ።
19.3 A general meeting can be called if more than half of the members request it.
አንቀጽ 20 Article XX
የዕድሩን መተዳደሪያ ደንብ ስለማሻሻልና መለወጥ
About amending and changing the by-law
የዋስትና ዕድር መተዳደሪያ ደንብ ዓላማውንና የተቋቋመበትን ተግባር እስካልተፃረረ ድረስ የካናዳ ህግ ከትርፍ ነጻ ለሆኑ ድርጅቶች ያወጣውን ህግ እስካልጣሰና ለማህበረሰቡና ለዕድሩ ዕድገት ጠቃሚ ሆኖ እስከተገኘ ድረስ የመተዳደሪያ ደንቡን እንደ አስፈላጊነቱ መቀየር ይቻላል፡፡ ለዕድሩ አባላትም ኮሚቴው ቤቱ የህጉን ማሻሻያ አንቀጽና ቁጥር ጠቅሶ እንዲያሳውቅ መተዳደሪያ ደንቡ ያስገድደዋል።
It is possible to amend the by-law as long as the objective and responsibility of the association are not altered. In addition, as long as it doesn’t breach the Toronto Law for non-profit organizations and as long as the amendment is beneficial to the betterment of the community and the association, it is possible to amend the bylaw as needed. The bylaw enforces the WMSA office to notify members of the amended article and number if any.
አንቀጽ 21 Article XXI
የዕድሩን የሥራ አስኪያጅ አባላትን በሕግ መጠየቅ የሚገልጽ ድንጋጌ
Rules providing immunity to the executive committee members of the WMSA
የዕድሩ የሥራአስኪያጅ ኮሚቴ በሙሉ ፈቃደኝነት ተመርጠው የሚሰሩ ግለሰቦች ናቸው። ምንም አይነት ክፍያም ሆነ ካሳ ከዕድሩ አያገኙም። ሆኖም እነዚህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎታቸውን በማበርከት ላይ ሌት ከቀን ለእድሩ ማደግና መሻሻል የሚጥሩ ናቸው ይሁንና ለዕድሩ ስራ ላይ ለሚፈጽሙት ከሥራቸው ጋር በተያያዘ ለሚፈጠረው ስህተት በህግ ተጠያቂዎች ናቸው።
All the officers in the executive committee are serving WMSA voluntarily and without any charge/wage. They will not get any kind of compensation from the Association. So, if these individuals/ officers commit any mistake while working for WMSA, they will be responsible from accountability.
አንቀጽ 22 Article XXII
ለዕድሩ ጠቃሚና ገንቢ የሆኑ አዳዲስ የአሰራር ሃሳቦችን ማመንጨት
Generating useful and new ideas for the betterment of WMSA
የዕድሩ ደንብና ህግ ሳይነካ ከዓላማው በተቃራኒ እስካልቀረበ ድረስ በማንኛውም ጊዜ ለአባላቶች ጥቅምና ለዕድሩ መጎልበት ሲባል ማሻሻያዎች ይደረጉበታል። ገንቢ ሃሳቦችንም ከአባላት ይቀበላል፡፡ የአስተዳደር ኮሚቴውም የራሱን ጠቃሚ ሃሳቦችን እያመነጨ ይሰራል።
As long as WMSA rules and regulations are not affected or ideas that are opposed to the objective of WMSA are not forwarded, changes that will benefit the members and strengthen WMSA will be appreciated. Members can also generate useful ideas and present them to WMSA. The administrative committee will also generate new ideas and implement them.
አንቀጽ 23 Article XXIII
የዕድሩ ጽህፈት ቤት አድራሻ
Address of WMSA’s Office
23.1 የዕድሩ ጽ/ቤት አድራሻ ————————————————————————-
23.1 Address of WMSA’s Main office ———————————————————–
23.2 ዕድሩ ለአባላት ይመች ዘንድ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት———————————————-
23.2 To make it convenient to members, branch offices will be located at ——————-
አንቀጽ 24 Article XXIV
የዕድሩ ድረ ገጽ
WMSA’s website: (www.wastena.org)
24.1 የመረዳጃ ዕድሩ ከሚጠቀምባቸው የመገናኛ ዘዴዎች ውስጥ አንዱ የማህበሩ ድረ ገጽ ነው፡፡ ይህንንም በተመለከተ የድረ ገጹ ሥምና አድራሻ ለአባላቱ በዝርዝር ይገለጻል።
24.1 One means of communications of WMSA its website. WMSA will disclose the name and address of the website to all members.
24.2 የማህበሩ ድረ ገጽ አጠቃቀምን በተመለከተ ለመመዝገቢያ ጣቢያነት ለሚረዱን የንግድ ድርጅቶች ማበረታታቻ ይሆን ዘንድ ነጻ የማስታወቂያ አገልግሎት ይሰጣል።
24.2 Regarding the use of the website, those businesses that are used as registration locations for WMSA will be provided with the opportunity to post their commercials on the website free of charge.
24.3 የዕድሩም አባላት ማንኛውንም የዕድሩን አገልግሎት በተመለከተ መረጃን፣ አስተያየቶችን መስጠትም ሆነ ማግኘት ይችላሉ።
24.3 Members can get information regarding the services of WMSA. They can also discuss their opinions if any.
24.4 የዕድሩ ድረ ገጽ የማንንም የፖለቲካ ድርጅት፣የሃይማኖትና የግለሰቦችን ጥቅም ሊያስገኝ ወይንም ሊያስከብር የሚችልን ማንኛውንም ማስታወቂያ አያስተናግድም፡፡የካናዳ ሕግ ነጻ የሆኑ ድርጅቶች ይህን እንዳያደርጉ ይከለክላል።
24.4 The website of WMSA will not post any advertisement/notices that would benefit individuals, political or religious organizations. Canadian law prohibits a non-profit organization from posting advertisements.
አንቀጽ 25 Article XXVI
የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላት የስራ ዘመን
Executive committee member’s tenure
25.1 የዋስትና ዕድር የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባል የስራ ዘመን 3 አመት ነው፡፡
251 Executive member’s terms of office will be three years.
25.2 የስራ ዘመናቸውን የፈጸሙ የስራ አስኪያጆች ጠቅላላ አባላት ባሉበት የመሸኛ ዝግጅት ተደርጎላቸው በአባልነታቸው ይቀጥላሉ። አዲሱ የስራ አስኪያጅ ችግር ሲያጋጥመው የስራ ልምዳቸውን በማካፈል በጋራ ይሰራሉ።
25.2 Those members who have completed their terms of offices will be recognized in the presence of all members at the end of their term and will continue to be members of WMSA and they will provide support to the new executive committee using their work experience as needed.
25.3 ማንኛውም የዕድሩ አባል የስራ ዘመኑን ቢጨርስም የዕድሩ አባላት ለቦታው አስፈላጊ መስሎ ከታያቸው እንደ አዲስ ሊመርጡ/ጧት ይችላሉ።
25.3 When any member of the executive committee completes his/her term in office, he/she can be reelected by members of WMSA as found fit.
25.4 የዋስትና መስራች የቦርድ አባላት ውስጥ አራቱ ተራ በመውሰድ ሥራ አስኪያጅ ኮሚቴው ውስጥ ተመድበው በየ3 ዓመቱ አዲስ ከሚመረጡት ጋር ያገለግላሉ።
25.4 The founders and bord member of WASTENA excuttive committee will take turn to serve every three year and will be assigned to work with the new elected bord member.
አንቀጽ 26 Article XXVI
የዕድሩ የመተዳደሪያ ደንብ የሚጸናበት ጊዜ
The validity of the by-law
ይህ መተዳደሪያ ደንብ ከ ዲሰምበር 3/2017 ቀን ጀምሮ የካናዳ ህግ በሚያዘው መሰረት ከትርፍ ነጻ በሆነ ድርጅትነት ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡ ስለዚህም የዋስትና የመረዳጃ ዕድር ተብሎ ይጠራል፡፡ በካናዳ የሀገር ውስጥ ገቢ ቢሮም በኩል በህጋዊነት ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
This by-law is valid from the day DEC3/2017where WMSA is registered as a nonprofit organization in accordance with the Canadian law. It is named as Wastena Mutual Support Association (WMSA) and it is lawfully registered with Canadian
Revenue Agency.
አንቀጽ 27 Article XXVII
እድሜው ከ 18 አመት በላይ የሆነ/ነች ማንኛውም የኦንታሪዎ ነዋሪ የአባልነት መመዝገቢያ ፎርሙን በመሙላት የነዋሪነት ማረጋገጫ ፎቶ ኮፒ እና ሁለት ጉርድ ፎቶግራፋ በመያዝ ቀርቦ መመዝገብ ይችላል።
To register you must be Ontario resident and age 18 and over. Please bring a copy of proof of ID that shows you are a resident of Ontario along with 2 passport size pictures.
For more info: Call
416-993-0551 , 416-827-0075 , 416-823-7934 , 647-869-0113